- ምስራቅ ማሞ እና ችስታ ባንድ፡ ጊዜ ቢያሳየኝም/ናኑ ናኑ ነይ
- መለሰ ቦንገር እና ችስታ ባንድ፡ ልቤ አንቺን አለና/እሪ ጉራጌ
- ትእግስት አሰፋ፡ ቱቱዬ
- አዳነ ተካ ፡ ቦብ ማርሌ
- አዳነ ተካ ፡ መድለይ
- ማለፊያ ተካ ፡ እንደ እየሩሳሌም
- አስፋው ክበበ ፡ አንቺ ሆዬው ለኔ
- አስፋው ክበበ ፡ ተመለሰ ባቡሩ
- ዘውዲቱ ዮሃንስ ፡ ቦለል
- የዝና ነጋሽ ፡ ሰቆጣ
- አዲሱ አባተ እና ትእግስት አሰፋ ፡ አምባሰል
- ጂሚ መሃመድ ፡ የህይወቴ ህይወት
- ጂሚ መሃመድ በጣም ጎበዝ ባለ ድንቅ ድምፅ ማየት የተሳነው ሙዚቀኛ የነበረ ሲሆን ሁዋላ ላይ በ1999 እና 2000 በኔዘርላንዱ Terp Records (The Ex Band) አማካይነት “ተቀበል” እና “ሁልጊዜ” የተባሉ ሁለት አልበሞችን አውጥቶ ነበር:: ጂሚ በ1999 አ.ም ነበር ህይወቱ ያለፈው:: ሁለተኛ አልበሙም የወጣው እሱ ካለፈ በሁዋላ ነበር (ነፍስ ሄር))
- መለሰ አስማማው እና ትጋው በለጠ ፡ ኢትዮጵያ ሃገሬ
ይህ ኢትዮጲክስ 2 “ተጫወት” አልበም የተቀረፀው በጥቅምት ወር 1989 አ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን አልበሙን የቀረፀው ደግሞ Philippe Gasnier ወይም Phil Gaz በሚለው የአርቲስት ስሙ የሚታወቀው የፈረንሳዩ ሬከርዲንግ አርቲስት ነው::
የአልበሙን ሚክሲንግ ደግሞ የሁሉም ኢትዮጲክስ አልበሞች ፕሮዲውሰር የሆነው Francis Falceto ከPhilippe Gasnier እና Wilfrid Harpaillé ጋር በመሆን ሰርተውታል:: ማስተሪንጉም የተሰራው ንብረትነቱ የWilfrid Harpaillé በሆነው Digital Edge ስቱዲዮ ነው::

Leave a comment