Various ‎– Éthiopiques 5: Tigrigna Music 1970-1975

2–3 minutes

To read


Various ‎– Éthiopiques 5: Tigrigna Music 1970-1975
  1. ፀሃይቱ በራኺ – አሚነይ
  2. ፀሃይቱ በራኺ – መጀመሪያ ፍቅረይ
  3. ፀሃይቱ በራኺ – ሃደረይ
  4. ፀሃይቱ በራኺ – ባዛይ
  5. ተወልደ ረዳ – መሞና
  6. ተወልደ ረዳ – ሚለኑ
  7. ተበረህ ተስፋ ሁነኝ – አደይ ወላዲተይ
  8. ተበረህ ተስፋ ሁነኝ – ወላድካ ሃዚለ
  9. ተወልደ ረዳ – አብ ተቃ ቅረቢ
  10. ተወልደ ረዳ – ነሃዳር ዘይተውከን
  11. ብዙአየነ ዘገየ – ፉሩይቲ አይነ
  12. ብዙአየነ ዘገየ – ደቂ አደይ
  13. ብዙአየነ ዘገየ – ነፀላ ማይ ማይ
  14. በየነ ሃብቴ – እምቢ ላ
  15. በየነ ሃብቴ – ተፍቀረኒ ዘነበረት
  16. ተክሌ ተስፋ እግዚ -ኣባዲት
  17. ተክሌ ተስፋ እግዚ -ኣብ ቀትሪ ብርሃን
  18. ተክሌ ተስፋ እግዚ – ሰካም ተመኘዋት

በዚህ አልበም ላይ ከዘፋኞቹ ስም ያለፈ መረጃ ለማግኘት አልተቻለኝም:: Barnes & Noble የተባለው record distributer ድህረ ገፅ ላይ ካገኘሁት ከዚች ትንሽ ማስታወሻ በቀር:: ከሚቀር እንዳለ አምጥቼዋለሁ::

ተክሌ ተስፋ እግዚ – አቀናባሪ, መሳሪያ ተጫዋች, ድምፃዊ
ተበረህ ተስፋ ሁነኝ- መሳሪያ ተጫዋች እና ድምፃዊ
ብዙ አየነ ዘገየ – መሳሪያ ተጫዋች እና ድምፃዊ
በተጨማሪም ፀሃይቱ በራኺም በክራር መሳተፉዋን አውቃለሁ:: ተጨማሪ የምታውቁት ካልችሁ ጨምሩበት:: እንዲሁም ትግርኛ ተናጋሪ ካለ የቃላት ግድፈት ማረም ይቻላል:: ብዙዎቹን በግምት ነው የፃፍኩዋቸው ከእንግሊዝኛው ወደ አማርኛው ፊደላት::

ስለ ፀሃይቱ ካነሳን አይቀር አንድ ክስተት ላጫውታችሁ::

ፀሃይቱ የተወለደችው በ1931 አ.ም በያን ጊዜው የኤርትራ ግዛት (በአሁኑ አርትራ ሃገር 😋) ቋቲት በተባለ ስፍራ ነው:: ሙዚቃ መጫወት የጀመረችው ደግሞ ገና ትንሽ ልጅ እያለች በ8 አመቷ ነበር:: ሙዚቃ ስንል ደግሞ መዝፈን ብቻ አልነበረም:: ክራር ከበሮ እና ቤዝ ክራር በመጫወት ባለብዙ ተሰጥኦ መሆኑዋን ከማስመስከርም አልፋ በየምሽት ቤቶችና እንደ ሰርግ ባሉ ማህበራዊ ክዋኔዎች ላይ በመጫወትም ተወዳጅነትን አትርፋለች:: በ1952 አካባቢ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከተወልደ ረዳ ጋር ሆና በፊሊፕስ አማካይነት የመጀመሪያ ሙዚቃዋን ለማሳተምም በቅታ ነበር:: ወደ ፀሃይቱ ለኤርትራውያን ትልቅ ትርጉም ያላት ተወዳጅና እውቅ ሙዚቀኛ ነች:: ታድያ እንደምናውቀው ኤርትራ ውስጥ ያለውን አፋኝ የመንግስት ስርአት ሽሽት ወደስደት በማቅናት በሱዳን በኩል አድርጋ ሁዋላ ላይ በ1980 አ.ም ሆላንድ ሃገር ሮተርዳም ገብታለች::


ይህም እንደ መግቢያ አልኩ እንጂ ከላይ ልንገራችሁ ያልኩት ክስተት የተፈጠረው እንግዲህ ሆላንድ ሃገር ነው::
ስለ ኢትዮጲክስ 2 ስናነሳ ጂሚ መሃመድ የተባለው ማየት የተሳነው ድምፃዊ ሆላንድ ሃገር በሚገኘው Terp Records/The Ex Band አማካይነት ሁለት አልበም አሳትሞ ነበር አላልኩዋችሁም ነበር? እናማ በአንድ አጋጣሚ የዚህ ሬከርድ ሌብል ባለቤት የሆነው Terrie Hessels ፀሃይቱን በሆነ አጋጣሚ ያገኛታል እናም ስለሱዋ ያውቃል:: እንዲሁም ሙዚቃ መጫወት እንዳቆመች እና ከተጫወተችም ረጅም አመት እንደሆናት ይጨዋወታሉ:: ከዚያማ በቃ ትውውቃቸው ወዳጅነት ይመሰርትና ክራር ምናምን ሰርቶ ይሰጣትና በአዲስ መልክ ሙዚቃ መጫወት እንድትጀምር ያደርጋታል:: በዚህ ብቻም አላበቃም በተለያዩ ወቅቶች ተጫውታቸው የነበሩ 17 ሙዚቃዎቿን በአዲስ መልክ እንድትጫወታቸው አድርጎ ባለሁለት ሲዲ አልበም ሙሉ የህይወት ታሪኳን ከያዘ ቡክሌት ጋር “ሰላም” በሚል መጠሪያ አሳትሞላታል::

ፀሃይቱ በራኺ ከዛሬ ሁለት አመት በፊት በ2010 አ.ም ነበር በሮተርዳም ኔዘርላንድስ ህይወቷ ያለፈው::

Leave a comment

Ama Ndlovu explores the connections of culture, ecology, and imagination.

Her work combines ancestral knowledge with visions of the planetary future, examining how Black perspectives can transform how we see our world and what lies ahead.