
- አባታችን ሆይ
- መዲና እና ዘለሰኛ
- ተው ስማኝ ሃገሬ
- የእመቤታችን ሰላምታ
- ከቶ አይቀርም ሞቱ
- ስለ ስነ ስቅለት
7.አባ ግራኝ ሞተ - ስለ ስነ ፍጥረት
- ዳግም ምፅኣት
10.ስለ ገና - ማን ይመራመር?
- የበገና ድርደራ
ይህን አልበም የቀረፀው Jean-Christophe Meissonnier በተባለ ፈረንሳያዊ የሳውንድ ኢንጅኒር ሲሆን የተቀረጸው ደግሞ Artistic Palace በተባለ ደቡባዊ ፈረንሳይ ቦሎኝ ከተማ ውስጥ ባለ ቦታ ነው:: የኢትዮጲክስ አልበሞች ውስጥ ይህና ሌሎችም ጥቂት አልበሞች በፍራንሴስ ፋልሴቶ አማካይነት ኦሪጅናል ስራ ሆነው ተቀርፀዋል::
ቅድመ ማስተሪንግ: Capitaine Fracasse
ማስተሪንግ: Top Master
ጋሽ አለሙ አጋ የተወለዱት በ1942 አ.ም አዲስ አበባ እንጦጦ ሲሆን በገና መማርና መጫወት የጀመሩት ገና በ12 አመታቸው ነው:: በገና መጫወትን የተማሩት ደግሞ ጎረቤታቸው እንዲሁም በሚማሩበት ትምህርት ቤት መምህር በነበሩት የበገና ሊቅ ተብለው ከሚጠሩት አለቃ አለማየሁ ወልደ አማኑኤል ዘንድ ነው::
ጋሽ አለሙ አጋ ከበገና ጨዋታ ላይ እንዲሁም መንፈሳዊው አለም ላይ ካላቸው ተሳትፎም በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በጂኦግራፊ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን እንዲሁም በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት እስከ 1972 አ.ም ድረስ የበገና መምህር በመሆንም አገልግለዋል::ጋሽ አለሙ አጋ ይህን የኢትዮጲክስ 10ኛውን የሙዚቃ ሰንዱቅ ጨምሮ የተለያዩ የበገና ጨዋታ አልበሞችን ያሳተሙ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች አይነት የሙዚቃ አልበሞች ላይም ተሳትፈዋል:: (የበርካታ አርቲስቶች ስራዎች በስብስብ የቀረቡባቸው አልበሞች ላይ)
ከስራዎቻቸው ውስጥ ጥቂቶቹ
Alèmu Aga – Éthiopiques 11: The Harp Of King David 1987
Asnakech Worku & Alemu Aga – Ende Jerusalem 1988
The begenna of elders – The harp of David in Ethiopia 2001
Ethiopia – Bagana Songs (Éthiopie Les chants de bagana) 1998
Alemu Aga – Ethiopia (Three Chordophone Traditions) 1966
Leave a comment