Ali Mohammed Birra ‎– Éthiopiques 28: Great Oromo Music

  1. Awash
  2. Kan Ati Fettun Isani Infedhani
  3. Nagatti Si Jedha
  4. Imiman Jalaala
  5. Eshurruru
  6. Waa Silleen Indararu
  7. Awash
  8. Eessaati Si Arga
  9. Si Jaalalle
  10. Abbaa Lafa
  11. Inyaadi’ini
  12. Si Inhabisin Warri – 1965
  13. Yaa Hundee Bareedaa
  14. Awash (በድምፅ እና ጊታር ብቻ)
  15. Si Jaalallee ከክቡር ዘበኛ ባንድ ጋር

ይህ 28ኛው የኢትዮጲክስ አልበም የወጣው በ2005 አ.ም ሲሆን በዚህ አልበም ላይ የተካተቱት ሙዚቃዎች የተሰሩት ደግሞ
ሙዚቃ ቁጥር 1 እና 12 በ1965 አ.ም
ከቁጥር 2 – 11 ያሉት ሙዚቃዎች በ1967
ሙዚቃ ቁጥር 13 እና 14 ደግሞ በ1950ዎቹ አጋማሽ ላይ ሲሆን ቁጥር 15 ደግሞ በ1958 አ.ም አካባቢ ነው::

በ1939 አ.ም በድሬዳዋ ገንደ ቆሬ በተባለ ቦታ የተወለደው አሊ ቢራ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ስማቸው ጎልተው ከሚነሱ አንጋፋ ድምፃውያን አንዱ ሲሆን የተለያዩ አይነት ሙዚቃዎቹን በኦሮምኛ አረብኛ ሀደርኛ ሶማልኛ እና አማርኛ ቋንቋዎች ተጫውቷል:: አሊ ቢራ ሙዚቃ መጫወት የጀመረው ገና በልጅነቱ ሲሆን በ14 አመቱ ነበር የኦሮሞን ባህልና ሙዚቃ ለማስተዋወቅ የተመሰረተውን “አፍረን ቀሎ” የተባለውን የኦሮሞን ባህልና ሙዚቃ ለማስተዋወቅ የተመሰረተውን የሙዚቃ ቡድን የተቀላቀለው:: ታዲያ አፍረን ቀሎ የሙዚቃ ቡድን ውስጥ ይጫወት በጀመረበት ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጫወተው ሙዚቃ ” ቢራ ዳ ባሬ” የተባለው ነበር:: አሊ የተባለ ሌላ ድምፃዊ ስለነበር ሁለቱን አሊዎች አበባጁከሚጫወተው ቢራ ድ ባሬ የተባለው ሙዚቃ ላይ ቢራ የሚለውን በመውሰድ ነበር አሊ ቢራ የሚለው ስም የወጣለት እና እስከ ዛሬ የአርቲስቱ መጠሪያ ስም ሆኖ የቀረው:: አፍረን ቀሎ የሙዚቃ ቡድን በሚሰራቸው ስራዎች በ1958 አ.ም በመንግስት እገዳ ይጣልበትና የባንዱ አባላትም እየተፈለጉ ለእስር ይዳረጉ ስለነበር አሊ ቢራም በጊዜው ይህንን ሽሽት ወደ አዲስ አበባ ከተማ መጣ::

ታዲያ አሊ ቢራም በተለያዩ ቋንቋዎች መዝፈን ይችል ስለነበር አዲስ አበባ እንደመጣ በሙዚቃው ለመቀጠል ብዙ አልተቸገረም ነበር:: አዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ በሚሳተፍበት ወቅት ያገኘው የኦሮሞው ብሄርተኛ አህመድ ታቂ ጊታር ገዝቶ ስለሰጠው አሊ ቢራም ጊታሩን እየተጫወተና እየዘፈነ በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ ሙዚቃውን በማቅረብ መሳተፉን ቀጠለ:: በዚህ ወቅት ነበር በጊዜው የክቡር ዘበኛ ባንድ መሪ የነበሩትን አቶ እዩኤል ዩሃንስን የተዋወቀው እና ሁዋላም ላይ ክቡር ዘበኛን ለመቀላቀል የበቃው::

እንዲህ እንዲህ እያለ የጀመረው የአሊ ቢራ የሙዚቃ ታሪክ እጅግ ሰፊ ነው:: በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ የሚባለውን ኦሮምኛ የሙዚቃ አልበም ያሳተመውም አሊ ቢራ ነው በ1963 አ.ም:: ከዚያ ደግሞ በመቀጠል በጣም ተወዳጅ የሆኑለትን Hin Yaadin” “Asabalee” “Ammalelee” እና “Gamachu” የተሰኙትን ሙዚቃዎችም ሰርቶዋል::

አሊ ቢራ ከክቡር ዘበኛ የሙዚቃ ባንድ ከአለም ግርማ ባንድ ራሱ በመሰረተው አዱ ቢራ ባንድ እና ሌሎችም በርካታ ባንዶች ጋር በቁጥር የበዙ ተወዳጅ አልበሞችን ለህዝብ ያደረሰ ጉምቱ ሙዚቀኛ ነው::

ስለ አሊ ቢራ ተጨማሪ መረጃዎች እና ማስተካከያ ካለ በአስተያየት መስጫው ላይ ማስፈር ይቻላል::

··················

Comments

Leave a comment