1-01 መዲና
1-02 ትካስ
1-03 ምስጋና
1-04 ዘለሰኛ
1-05 የጃንሆይ ምስጋና
1-06 የራስ ወልደ ጊዮርጊስ
1-07 የራስ መኮንን
1-08 የሊጋባ
1-09 የእቴጌ
1-10 የአለም ምስጋና
1-11 የሞት ማስታወሻ
1-12 የነጋድራስ
1-13 የዘውዲቱ
1-14 አቶ ዮሴፍ
1-15 ደጃች ባልቻ
1-16 የትካዜ
1-17 የራስ ሚካኤል
1-18 ደጃች አባተ
1-19 የነጋድራስ
1-20 ደጃች ውቤ
2-01 ለኖሽ ሃመሩ
2-02 ኣዶ ወሸባ
2-03 የፍቅር
2-04 አያ ወሸባዬ
2-05 አልቦ ወሳጅ መስለክ
2-06 መልኪያዶም
2-07 ደማ ደማ
2-08 መኮንን
2-09 የተቃሰ
2-10 ስማ
2-11 እሰይ ና ና
2-12 ቧልት
2-13 ቃለ መጠይቅ ከይድነቃቸው ተሰማ ጋር 1976
2-14 ቃለ መጠይቅ ከይድነቃቸው ተሰማ ጋር 1976 -77
ይህ አልበም በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው በሸክላ ላይ የተቀረፀላቸው የአዝማሪው (ሁዋላም ላይ ነጋድራስ) ተሰማ እሸቴ የሙዚቃ አልበም ሲሆን በኢትዮጲክስ የሙዚቃ አልበሞች ስብስብ ላይ የተካተተውና የወጣው ደግሞ በ2003 አ.ም ነው:: የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ሙዚቃዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የታተሙት በ1902 አ.ም በአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግስት ሲሆን ይህም ከ110 አመታት በፊት በአፄ ምኒልክ አማካይነት ጀርመን ሃገር የመኪና ጥገና ለመማር በሄዱበት ወቅት ነው:: ሙዚቃዎቹን ያሳተመላቸው ደግሞ የበርሊኑ “ሂስ ማስተር ቮይስ” (HMV Germany) የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት ነበር:: እነዚህ ሙዚቃዎች ምናልባትም በአፍሪቃም የመጀመሪያዎቹ ሳይሆኑ እንደማይቀሩ ይገመታል::
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ከአዝማሪነት በተጨማሪ ቀራፂና ሰአሊ ፖለቲከኛ የፎቶግራፍ ባለሙያ ባለቅኔና የሌሎችም በርካታ ሙያዎች ባለቤት ነበሩ:: ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስም ካላቸው እና “The father of sport in Africa” ተብለው የሚጠሩት የክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አባት ናቸው::
እነዚህ የነጋድራስ ተሰማ እሸቴ ብርቅዬ ሸክላዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ውስጥ ተሰብስበው ይገኛሉ፡፡ እነዚህ በተቋሙ እጅ ያሉት 16 ያህል ሸክላዎች እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ዜማዎችን የያዙ ሲሆን በአጠቃላይ 32 ዜማዎች ተቀርፀውባቸዋል፡፡
ተጨማሪ ስለአዝማሪው ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ የአማርኛው ዊኪፔድያ ላይ ያገኘሁትን ፅሁፍ ላጋራችሁ::
ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ፥ከአባታቸው፡ከአቶ፡እሸቴ፡ጉቤ፡ከጐጃም፡በረንታና፡ከቦረና፡ጨከታ ፡ከናታቸው፡ከእማሆይ፡ወለተየስ፡ሀብቱ፡ከቡልጋ፡መስኖ፡ማርያም፡ይወለዳሉ።
የተወለዱት፥ሐምሌ ፳፡ቀን፥፲፰፻፷፱፡ዓ.ም.፥ምንጃር፡ቀርሾ፡ዐጥር፡በተባለው፡ስፍራ፡ነው።አባታቸው፡አቶ፡እሸቴ፥የራስ መኰንን፡ ጭፍራ፡ስለ፡ነበሩና፥መሰንቆም፡ስለሚጫወቱ፥ራስ፡መኰንንን፡ተከትለው፡ወደ፡ሐረር፡ሲኼዱ፥ነጋድራስንም፡በሕፃንነታቸው፡ይዘዋቸው፡ስለ፡ኼዱ፥ያደጉትና፡ዐማርኛ፡ትምህርታቸውን፡ያጠናቀቁት፡በሐረር፡ነው።
አባታቸው፡አቶ፡እሸቴ፥ሐረር፡እንዳሉ በመሞታቸው፥ነጋድራስ፥በወጣትነት፡ዕድሜ፥ዳግማዊ ዐፄ፡ ምኒልክን፡ተከትለው፡ወደ፡አዲስ አበባ፡መጡ።
በ፲፱፻፡ዓ.ም.፥ሙሴ፡ሆልስ፡የተባለ፡ጀርመናዊ፡በኢትዮጵያ፡ለብዙ፡ጊዜ፡ከቈየ፡በኋላ፥ወደ፡አገሩ፡ሲመለስ፥ዐፄ፡ምኒልክን፡በተሰናበተበት፡ጊዜ፥ጀርመን፡አገር፡ወስዶ፡የሚያስተምራቸው፡ሦስት፡ወጣቶች፡እንዲሰጡት፡ስለ፡ጠየቃቸውና፥ነጋድራስ፡ተሰማ፡እሸቴም፡በጥሩ፡ሠዓሊነታ ቸው፡በቤተ፡መንግሥቱ፡ስለ፡ታወቁ፦«ያ፡ተሰማ፡እሸቴ፥እጁ፡ብልኅ፡ነውና፥መኪና፡መንዳት ና፡መጠገን፡እንዲማር፡እሱ፡ይኺድ»፡ብለው፡ዐፄ፡ምኒልክ፡ስለ፡ወሰኑ፥ወደ፡ጀርመን፡አገር፡ለመኼድና፥ለኹለት፡ዓመት፡ያኽል፡የኦቶሞቢልን፡አሠራር፡ለመማር፡ቻሉ።
ነጋድራስ፥መሰንቆ፡መምታትና፡ዜማ፡ካባታቸው፡ተምረው፡ስለ፡ነበር፥ወደ፡ጀርመን፡አገር ፡ኼደው፡በቈዩበት፡ጊዜ፥ የተላኩበትን የሹፌርነትና የመካኒክነት ትምህርት አጠናቀው አጥጋቢ ውጤት ከማምጣታቸውም በላይ የመጀመሪያውን የአማርኛ ዜማ ሸክላ እዚያው በጀርመን ሀገር ሆነው ለማስቀረፅ በቅተዋል። በጀርመን ቆይታቸው ወቅት “ሂዝ፡ማስተርስ፡ቮይስ”፡ከሚባለው፡ኩባንያ፡ጋራ፡በመዋዋል፥መዲናና ዘለሰኛ ዜማዎች በ፲፯ አይነት ስልት እየተጫወቱ ተቀርፀዋል። ኩባንያውም ለዜማው ባለቤት የድካም ዋጋ እንዲሆን በወቅቱ ፲፯ ሺህ የጀርመን ማርክ ከፍሏቸዋል። ይህም፥ዐዲስ፡አበባ፡ሲመለሱ፥በሀብታሞች፡ደረጃ፡ለመቈጠር፡ዕድል፡ሳይሰጣቸው፡ አልቀረም።
ነጋድራስ፡ተሰማ፡እሸቴን፡እጅግ፡ታዋቂ፡ካደረጓቸው፡ነገሮች፡አንዱ፥የነዚህ፡ዲስኮች፡ ኢትዮጵያ፡መምጣትና፥ሌላም፡ያማርኛ፡ዲስክ፡ስላልነበረ፥ለኻያ፡ዓመት፡ያኽል፥ዐቅም፡ባለው፡ቤተሰብ፡ዅሉ፡በግራሞፎን፡ይሰማ፡የነበረው፡የሳቸው፡ዘፈን፡ብቻ፡በመኾኑ፡ነው።ሌሎች፡ያማርኛ፡ዲስኮች፡የተቀረጹት፡ጠላት፡ኢትዮጵያ፡ሊገባ፡ኹለት፡ዓመት፡ያኽል፡ሲቀር ፥በነፈረደ ጐላ፥በነንጋቷ ከልካይና፡በነተሻለ መንግሥቱ፡ተጫዋችነት፡ወደ፡፲፱፻፳፭-፲፱፻፳፮፡ገደማ፡ነው።
ዐዲስ፡አበባም፡እንደ፡ተመለሱ፥የቤተ፡መንግሥት፡መኪናዎች፡ኀላፊ፡ኾነው፥የዘመኑን፡ታዋቂ፡ኢትዮጵያውያን፡ሾፌሮች፡አሠልጥነዋል።
ስለ፡ዐፄ፡ምኒልክ፡በተጻፈ፡አንድ፡የታሪክ ፡መጽሐፍ፡ላይ፥ነጋድራስ፡መኪና፡ላፄ፡ምኒልክ፡ሲያሳዩ፡የተነሡት፡ፎቶግራፍ፡አለ።ጸሓፊው፡ግን፥በስሕተት፥”ፈረንጅ፡ሲያስጐበኝ”፡ብሎ፡ጠቅሶታል።
Leave a comment