- ትዝታ
- ና ገዳሙ
- ፋኖ
- ገለል
- የሙዚቃ ሞገስ
- ብርቱካኔ
- ሳተናው
- እባክሽ ታረቂኝ
- አንቺ ሆዬው ለኔ
- ጉም ጉም
- ውብዬ
- ኧረ ጎራው
- መገን ያራዳ ልጅ
ካሳ ተሰማ በተለይም በክራር ጨዋታ ታጅበው በተሰሩ ሙዚቃዎቹ ይታወቃል:: ሙዚቃዎቹ ስሜት ቀስቃሽ ዜማዎችን (melancholic melodies) የያዙ እና እና የዘመኑን የሙዚቃ ባህል እና መልክ የሚያሳዩ ከመሆናቸውም በተጨማሩ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ ግጥሞችን የያዙና በዘመኑ የነበረውን ለአዝማሪዎች ብቻ የተሰጠ ይመስል የነበረውን ሃሳብን በነፃነት የመግለጥ መብት የሚያንፀባርቁም ናቸው :: በዚህ አልበም ላይ የተካተቱት ሙዚቃዎች አብዛኞቹ በ1964 እና 1968 አ.ም በፊሊፕስ ኢትዮጵያ አማካይነት ከታተሙት ሁሉት LP ሸክላዎች ላይ የተወሰዱ ሲሆኑ ይህ የኢትዮጲክስ 29 አልበም የወጣው ደግሞ በ2008 አ.ም ነው::
ካሳ ተሰማ በ1934 አ.ም በደጃች ወንድይራድ የሙያ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት (የአሁኑ ተግባረ እድ) የቧንቧ ስራ ትምህርትን ተምሮ ነበርና ትምህርቱን ሲጨርስ የተቀጠረው የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራ ውስጥ በቧንቧ ጠጋኝነት ነበር :: ከዚህ ተነስቶ ነው እንግዲህ የኦርኬስትራው ተወዳጅ ድምፃዊ ለመሆን የበቃው::
ስለካሳ ተሰማ የህይወት ታሪክ ብዙም ተፅፎ አይገኝም:: እስቲ ስለ ካሳ ተጨማሪ የምታውቁት መረጃ ካለ አክሉበት::
Leave a comment