Tsegué-Maryam Guèbrou ‎– Éthiopiques 21: Piano Solo

Tsegué-Maryam Guèbrou ‎– Éthiopiques 21: Piano Solo
  1. The homeless wanderer
  2. The last tears of a deceased
  3. A young girls compliant
  4. The mad mans laughter
  5. Presentiment
  6. Mother’s love
  7. Ballad of the spirits
  8. The song of the sea
  9. Homesickness
  10. Golgotha
  11. The Jordan river song
  12. The garden of Gethesemani
  13. The song of Abay
  14. The story of the wind
  15. Evening breeze
  16. Tenkou! Why feel sorry?

እነዚህ ሙዚቃዎች ከተለያዩ የእማሆይ አልበሞች ላይ ተሰባስበው በኢትዮጲክስ 21 ላይ በድጋሚ የታተሙት በ1998 አ.ም ሲሆን እነዚህ ሙዚቃዎች ኢትዮጲክስ አልበም ላይ ከመግባታቸው በፊት

  • ከሙዚቅ ቁጥር 1-5 ያሉት ሙዚቃዎች በ1959 አ.ም ጀርመን ሃገር ካሳተሙት “Spielt Eigene Kompositionen” LP
  • ከቁጥር 6-9 ያሉት ሙዚቃዎች ደግሞ በ1955 አ.ም ካወጡት “Der Sang Des Meeres” LP
  • ሙዚቃ ቁጥር 10,11 እና 12 ደግሞ በ1962 ከወጣው The Hymn Of Jerusalem, The Jordan River Song አልበማቸው እና
  • የተቀሩት ከቁጥር 13-16 ያሉት ሙዚቃዎች ደግሞ በ1988 ከወጣው “Best of” ከተባለው በሲዲ ከወጣው ስራቸው ላይ የተውጣጡ ናቸው::

እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ ማን ናቸው?

ከሰዋሰው ድህረ ገፅ ላይ ቀንጨብ ያረኩትን ላካፍላችሁ::

በ1940 አመተ ምህረት በምንኩሥና ስማቸው ፅጌማርያም ተብለው መጠራት እስከጀመሩበት ድረሥ “የውብዳር” በሚባለው የአለም ስማቸው ይታወቁ ነበር። እማሆይ ፅጌማርያም የከንቲባ ገብሩ ልጅ እና በኢትዮጵያ ደራሥያን ታሪክ መልካም ሥም ያላቸው የወይዘሮ ሥንዱ ገብሩ እህት ናቸው። እማሆይ ፅጌማርያም ከአባታቸው ከከንቲባ ገብሩ ደሥታና ከእናታቸው ወ/ሮ ካሣየ የለምቱ በታህሣሥ ወር 1916 አመተ ምህረት አዲስ አበባ ውስጥ ተወለዱ። ዘመናዊ ትምህርታቸውን ከእህታቸው ከስንዱ ገብሩ ጋር የተማሩት በሥዊዘርላንድ እና በሌሎች አውሮፓ ሃገሮች ነው። እማሆይ ከውጭ ሃገር ቇንቇዎች እብራይስጥኛ፣ ፈረንሣይኛና ጀርመንኛ ቇንቇዎችን ከአማርኛ ባልተናነሠ እንደሚናገሩ ተፅፎላቸዋል። እማሆይ ፅጌማርያም ልዩ የሚያደርጋቸው የረቂቅ ሙዚቃን በሚገባ አጥንተው እሥከ ዘጠና እድሜያቸው ድረሥ ለመጫወት መቻላቸው ነው። እማሆይ ከመነኮሡ በሇላ አብዛኛውን ጊዜያቸውን በእየሩሣሌም ቢኖሩም የረቂቅ ሙዚቃን ኮንሠርት ከማቅረብ የቦዘኑበት ጊዜ የለም ለማለት ይቻላል። እማዮይ በእድሜ ዘመናቸው ብዙ አልበሞችን አቀናብረው አሣትመዋል። የረቂቅ ሙዚቃዎቻቸውን የሚያቀርቡበት በሚገባ ባጠኗቸው የፒያኖ እና የቫዮሊን መሳሪያዎች አማካኝነት እንደሆነ ታሪካቸው ያሥረዳል። “ኢትዮ ፒክ” በሚል መጠሪያ የሚታወቀው የመጨረሻ አልበማቸው ከቀድሞ ቅንብራቸው የተመረጡ ስራዎች የተካተቱበት እንደሆነ ታውቇል።

··················

Comments

Leave a comment