ጌታቸው ካሳ – “ብቻዬን ተክዤ” እና “በይ ልሰናበትሽ”

1–2 minutes

To read

ዛሬ ደግሞ በአምሃ ሬከርድ የወጣውን የጌታቸው ካሳን ሁለት ግሩም ሙዚቃዎች የያዘ ሌላ 7″ ሸክላ ይዘናል::

A. ብቻዬን ተክዤ

B. በይ ልሰናበትሽ

ድምፃዊና ግጥም ደራሲ – ጌታቸው ካሳ

ሙዚቃዎቹን ያቀናበሩት እና የተጫወቱት – ሶል ኤኮስ ባንድ

ይህ ሸክላ የወጣበት ዘመን – 1962 አ.ም

አሳታሚ – አምሃ ሬከርድስ (አምሃ እሸቴ)

አከፋፋይ – ሃራምቤ ሙዚቃ ቤት

ሶል ኤኮስ ባንድ ሙዚቀኞች

ቤዝ – ፈቃደ አምደመስቀል

ጊታር – አሉላ ዮሃንስ

ድራም – ተስፋዬ መኮንን

ኦርጋን (ኪቦርድ) – ተሾመ ምትኩ

ቴነር ሳክስፎን – ቴዎድሮስ ምትኩ

ትራምፔት -ታምራት ፈረንጅ

እነዚህ ሁለት ሙዚቃዎች ሁዋላ ላይ የኢትዮጲክስ ስብስቦች ላይ ተካተዋል:: ብቻዬን ተክዤ – éthiopiques-8: Swinging Addis 1969-1974 ላይ ታገኙታላችሁ::በይ ልሰናበትሽ ደግሞ – éthiopiques-24: Golden Years of modern Ethiopian music 1969-1975 ላይ ይገኛል::

በነገራችን ላይ “በይ ልሰናበትሽ” የተባለው ሙዚቃ የዘመኑን የቁዘማ ወይም የሃዘን ድባብና ትዝታ ውስጥ የሚከት የዜማ ስልት ( melancholic singing) በደምብ የሚያሳይ ነው:: የዜማው አሳዛኝነት እና የግጥሙ ሃሳብ እንዴት እንደተስማሙ ሳስብ ሁሌም ይደንቀኛል::

ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ!!

Leave a comment

Ama Ndlovu explores the connections of culture, ecology, and imagination.

Her work combines ancestral knowledge with visions of the planetary future, examining how Black perspectives can transform how we see our world and what lies ahead.