“ይበቃኛል” – ግርማ በየነ እና “የግሌ ትዝታ” -ሙላቱ አስታጥቄ

1–2 minutes

To read

ወጣትነት ማቆሚያ የሌለው እምቅ አቅም የሚሰጠን ድንቅ ነገር ነው:: በዚያ ላይ ደግሞ የታደሉት ወደውስጣቸው የሚያዩበት የተደበቀ ስጦታና ፀጋቸውን የሚያወጡበት የጉብዝና ዘመንም ነው:: በወጣትነት ዘመን ላይ ያለን “በዘመኔ ምን እየሰራሁ ነው?” ብለን ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል:: ዘወትር ወጣትና ባለትኩስ ሃይል ሆኖ መቆየት አይቻልም:: እድሜ ይገፋል ጉልበትና አቅምም ይደክማልና:: ከምክር ስንወጣ ደግሞ ቆየት ወዳለ የሙዚቃ ዳሰሳ እንሄዳለን::በዚህ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ባለ ሁለት ጥንድ ሙዚቃዎች 7″ ሸክላ በአምሃ እሸቴ አማካኝነት ከወጡ የዘመኑ ሙዚቃዎች 160ኛው ሰንዱቅ ነው:: ፎቶው ላይ የምታዩዋቸው ደግሞ The Timeless Ethiopian music pioneers ሙላቱ አስታጥቄ እና ግርማ በየነ ናቸው:: (በወጣትነት ዘመናቸው)በዚህ ሸክላ ላይ ያሉ ሙዚቃዎች ደግሞ A. ይበቃኛልድምፃዊ – ግርማ በየነግጥምና ዜማ ደራሲ – ባህታ ገብረ ህይወትየሙዚቃ ቅንብር – ግርማ በየነይህ ሙዚቃ ሁዋላ ላይ በፍራንሲስ ፋልሴቶ አማካኝነት ከወጡት የኢትዮጲክስ የሙዚቃ አልበሞች ስብስብ መሃል አንዱ በሆነው ኢትዮጲክስ 8 (‘éthiopiques-8: Swinging Addis) ላይ ተካቶዋል::B. የግሌ ትዝታ (በመሳሪያ የተቀነባበረ ሙዚቃ)ሙዚቃ ድርሰት እና ቅንብር – ሙላቱ አስታጥቄይህኛውም ሙዚቃ ኢትዮጲክስ 4 አልበም ላይ ሙሉ የሙላቱ አስታጥቄን ስራዎች የያዘው éthiopiques-4: Ethio Jazz የተባለው አልበም ላይ በመካተት በድጋሚ ለአድማጭ የበቃ ስራ ነው::ይህ ሸክላ

ዘመኑ ደግሞ በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በ1961 አ.ም ነው::

Leave a comment

Ama Ndlovu explores the connections of culture, ecology, and imagination.

Her work combines ancestral knowledge with visions of the planetary future, examining how Black perspectives can transform how we see our world and what lies ahead.