ማህሙድ አህመድ – “ኤቦ ላላ” እና “እሰት መራ”

1–2 minutes

To read

ኤቦ ላላ

ድምፃዊ – ማህሙድ አህመድ

ግጥምና ዜማ – ስዩም ባሩዳ

የሙዚቃ ቅንብር እና መራሄ ሙዚቃ – ኮሎኔል ሃይሉ ወልደማርያም

ሙዚቃ ጨዋታ – የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራ

ድምፃዊ – ማህሙድ አህመድ

እሰት መራ

ግጥምና ዜማ – ማህሙድ አህመድ

የሙዚቃ ቅንብር እና መራሄ ሙዚቃ – ኮሎኔል ሃይሉ ወልደማርያም

ሙዚቃ ጨዋታ – የክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራ

ሰሞኑን የፊሊፕስ ኩባንያን ስራዎች እየዳሰስን እንከራርማለን:: ለዛሬ ደግሞ በዚሁ በፊሊፕስ ኩባንያ ከወጡ ስራዎች መካከል 145ኛ የሆነውና በክቡር ዘበኛ ኦርኬስትራ ሙዚቀኞች በተለይም በዚሁ ኦርኬስትራ በርካታ ሙዚቃዎችን በመድረስ በማቀናበርና ኦርኬስትራውን በመምራት (በኮንዳክተርነት) ትልቅ አበርክቶ ያላቸውን የኮሎኔል ሃይሉ ወልደማርያምን 2 ቅንብሮችን የያዘው ይህ 7″ ሸክላ የወጣው በ1964 አ.ም ነው:: በነገራችን ላይ ኮሎኔል ሃይሉ ወልደማርያም ባለፈው ታሪኩን ያጋራሁዋችሁ የሙዚቃ መምህር አቀናባሪ እና የሳክስፎን ተጫዋቹ የፈለቀ ሃይሉ አባት ናቸው::

እነዚህ ሁለት ሙዚቃዎች ሁዋላ ላይ በ2002 አ.ም ኢትዮጲክስ 26 (éthiopiques-26: Mahmoud Ahmed & Imperial Bodyguard Band) ላይ ተካተዋል::

ጥሩ ቀን ይሁንላችሁ::

ደማቅ ቢጫ ቀን

💛 💛 💛

Leave a comment

Ama Ndlovu explores the connections of culture, ecology, and imagination.

Her work combines ancestral knowledge with visions of the planetary future, examining how Black perspectives can transform how we see our world and what lies ahead.